Rihanna x Manolo Blahnik “Rih-vi’s.
ይህን ያውቁ ኖሯል? በውክልና ከዚህ በታች የእርስዎ ተወካይ እርስዎን በመወከል ማከናወን እንደሚችል
- በስምዎ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ተወካይ እንደ እንዲጠብቁ፣እንዲቆጣጠሩ፣ እንዲያስተዳድሩ፣ እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ፣ እንዲያከራዩ፣ እንዲያኮናትሩ፣ ውል እንዲዋዋሉ፣ገንዘብና ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ፣
- አዲስ የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ፣ የተከፈተውንም የባንክ ሂሳብ እንዲያንቀሳቅሱ፣ ገንዘብ እንዲያስገቡ፣እንዲያወጡ፣ ቼክ ፈርመው መስጠትም ሆነ መቀበል እንዲችሉ፣
- ጨረታ እንዲጫረቱ፣ የጨረታ ውል እንዲዋዋሉ፣
- የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እነዲገዙ፣ ስሙን እንዲያዛውሩ፣ ሊብሬ እንዲያዎጡ፣ ቦሎ ከላውዶ እንዲያስደርጉ፣
- በማህበር ተደራጅተውም ሆነ በሊዝ ቦታ ተመርተው ቤት እንዲሰሩ፣ የግንባታ ፍቃድ እንዲያዎጡ፣ ግንባታዎችን እንዲያካሂዱ፣ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል እንዲረከቡ፣ ስብሰባዎች እንዲሰበሰቡ፣ ድምፅ እንዲሰጡ፣ የአባልነት መታዎቂያ እንዲያዎጡ፣ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ካርታ ፕላን፣ የፕላን ማሻሻያ እንዲያወጡ፣
- መብራት፣ ውሃ ስልክ እንዲያስገቡ፣ የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣
- ከውጭ የሚጣውን ማንኛውንም አይነት እቃም ሆነ መኪና በሚመለከተው የግምሩክ መ/ቤት በመቅረብ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በማሟላት መረከብ እንዲችሉ፣
- ሰሌዳ እንዲያስቀይሩ፣ ሊብሬ እንዲያወጡ፣
- የንግድ ፈቃድም ሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያዎጡ፣ እንዲያድሱ፣ አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ተመላሽ እንዲያደርጉ፣ የንግድ ዘርፉን እንዲለውጡ፣
- አክስዮን እንዲገቡ፣ ኩባንያ እንዲያቋቁሙ፣ በመመስረቻ እና በመተዳደሪያ ጉባኤ ላይ እንዲፈርሙ፣ ስብሰባዎችን እንዲሰበሰቡ፣ ድምፅ እንዲሰጡ፣ የአክስዮን ድርሻዎትን እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ፣ እንዲገዙ፣
- ከማንኛውም የትምህርት ተቋም በመቅረብ ማንኛውንም የትምህርት ማስረጃዎትን እንዲቀበሉ፣ የትምህርት ማስረጃዎትን ከሚመለከተው ክፍል እንዲያዎጡ፣ ሰነድ ላይ ፈርመው መስጠትም ሆነ መቀበል እንዲችሉ፣
- የልደት ወረቀት እንዲያወጡ
- የጉዲ ፍቻ ውልን በተመለከተ እርስዎን ወክለው እንዲያስ
- በእጣም ሆነ በምዝገባ ማንኛውንም ጉዳይ እንዲመዘገቡ፣
- የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትዎን በዋስትና አስይዘው ከባንክም ሆነ ከአበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ እንዲበደሩ፣ የብድር ውል እንዲዋዋሉ፣
- በስምዎም ሆነ በንብረትወ ላይ ክስ ክርክር ቢነሳ ቢችሉ እራሳቸው ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ የህግ ጠበቃ ይዘው ለመከራከር፣ አቤቱታ ለማቅረብ፣ መልስ ለመስጠት፣ ይግባኝ ለማለት እንዲችሉ፣ ቃለ መሃላ ፣ አቤቱታ እንዲያቀርቡ፣ የውሳኔ ሰነዶችን እንዲቀበሉ፣ አፈፃፀም እንዲቀበሉ፣ አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ሌላ 3ኛ ወገን እንዲወክሉ፣ እንዲሽሩ፣
- በአጠቃላይ በመንግስታዊ መ/ቤትም ሆነ በህዝባዊ ድርጅቶች እንዲሁም በአስተዳደር መ/ቤት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢምባሲዎች፣ በግምሩክ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመብራት ሃይል፣ በስራና ከተማ ልማት ቢሮ፣ በቀበሌ፣ በክፍለ ከተማ፣ በኢትዮ ሞባይል መምሪያ፣ በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፣ በመሬት አስተዳደር በመቅረብ ጉዳዮትዎን በመከታተል እንዲፈፅሙና መወከል እንደሚችሉ
CHOOSE YOUR ORDER
Attention if you do not have a valid Ethiopian passport and if you are not an Ethiopian citizen you may need to have both the Amharic Wikilina and its English translation
Read more