Fake Ethiopian money :በሀሰተኛ ብር ጤፍ የገዙ ግለሰቦች መሰወራቸው ተገለፀ፡፡
በሀሰተኛ ብር ጤፍ የገዙ ግለሰቦች መሰወራቸው ተገለፀ፡፡
በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 በአዲሱ ጤፍ ተራ ላይ 7 ኩንታል ጤፍ በሀሰተኛ ብር ገዝተው መሰወራቸውን የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት የሆኑት ኢንስተፔክተር ደባሱ በላይ ለጽ/ቤታችን በላኩት መረጃ ገልፀዋል፡፡
ከተለያዩየ ገጠር ቀበሌዎች ጤፍ ለመሸጥ የመጡ አርሶአደሮችን በሀሰተኛ ብር 7 ኩንታል ጤፍ በ 10 ሺ 6 መቶ ብር በመግዛትና ጤፉን ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር የእጅ ጋሪ ጠርተው እህሉን ለማስጫን ሲሞክሩ አንዱ አርሶ አደር ብሩን በመጠራጠር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሄድ ብሩ የሀሰት ብር መሆኑን አረጋግጦ በፍጥነት እህሉን እንዳይጭኑት አስመልሰዋል፡፡
የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል መከላከል ግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን መሪ ምክትል ኢንስቴክተር አልማው ወርቅ የህብረተሰቡ እንደነዚህ ያሉ አጭበርባሪዎችን አጋልጦ ለህግ ሊያቀርባቸው ይገባል በማለት ማህበረሰቡ ከተለያዩ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል፡፡
ከደብረማርቆስከተማአስተዳደር
የመንግስትኢንፎርሜ
Read more