About GIRAR
ጤና ይስጥልን። እንኳን ወደ ግራር ሚዲያ Girarmedia ድረ ገፅ መጡ። ይህ ውጥን ከአስራ አምስት አመት(15 years) በላይ የፈጀ ሲሆን ይህንን አገልግሎት ስንሰጥ የመጀመሪያው አንጋፋ የኢትዮጵያ ድረ ገፅ ያደርገናል። ይህንን ፖሮጄክት የጀመርነው በ1999 ሲሆን ነገር ግን በተለያዩ አጋጣሚወች ድር ገፅችን በሀከሮች (hackers))ሲሰበር ኖሮ ዛሬ በአዲስ መልክ ስራችንን ጀምረናል። አላማችን የኢትዮጵያን ቪዲዮውችን እና በቪዲዮ ስራ ላይ የሚሰማሩትን ዘፋኞችን፣ ተዋናዮችን፣ ዳሪክተሮችን እና ሌሎችንም ግለስቦች ቋሚ ቦታ ለመስጠት ነው። ታዲያ ስራችንን በጣም የሚያቃልል ዘዴ ስለተገኘ ከእኛ ዘንድ ወይም ሰርቨር (severer) ምንም አይነት ቪዲዮ ሳንጭን ሁሉንም ቪዲዮዎች ከተለያዪ ቦታዎች ቃርመን ለእይታ እናበቃለን። ስለመጣችሁ እናመሰግናልን::
ለምን ግራር ተባልን? ለብዙ አመታት ለምናደርገው ውጥን ተገቢ ስም ለማግኘት ያልወጣንበት ያልወረድንበት ዳገትና ቁልቁላት የለም። ያኔ የኛን ስራ ስንጀምር ቪዲዮ እንኳን በኢንተርኔት ሊታይ ቀርቶ የተፃፈን ዜና እንኳ የምናንበው በስንት ግድ ነበር። የኢንተርኔት ፍጥነቱ በጣም ደካም ስለነበር አንድ ፎቶ ለማየት የሚወስደውን ጊዜ ያዬ ብቻ ያውቀዋል። ይህን የምንለው ገና ጉግልም ሆነ ዩቱብ ሳይፈጠሩ የፌስ ቡክ መስራች ህፃን ከመሆኑ የተነሳ ኢንተርኔት ማየት እንኳ በማይፈቀድለት ዘመን ነው። ያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ድረ ገፅ የሚባል ነገር ፈፀሞ አልነበረም። አልፎ አልፎ ኔትስኬፕ (Netscape) እና አንጅልፋዬር (Angle Fire) ከሚባሉ ገፆች የነፃ ድረ ገፆች ነበሩ። ታዲያ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሺ እነ ዩትብ ሲፈጠሩ የነሱን ኮድ አስመስሎ የሚሰራ ሌላ ድርጅት ነበር ነገር ግን ቪዲዮዎች በጣም ውስን ስለነበሩ እኛ ያለን አማራጭ እዚያው ዩቱብ (Youtube) ላይ ሆነን ሌላ ወብ ሳይት መፍጠር ነበር። ነገርግ ግን ያው የእጣ ፋንታ ሆኖ ምቀኞች ሳይቱን ብዙ ጊዜ እየገቡ ስላበላሹት (Hacked) እና ሌላም ከቪዲዮ ውጭ የነበረውን መረጃ ስላበላሹት ነገሮች ሁሉ ቦታ ቦታ እስከሚይዙ መጠበቅ ግድ ሆኖ ነበር። ዛሬ የኢንተርኔት ፍጥነት ተሻሽሎ፣ ዩቱብ ከ አስር ደቂቃ ቪዲዮ እስከ ፈለጉብት ሰዓት መጫን ተፈቅዶ፣ ከዩቱብ በላይ ሌሎችም ድረ ገፆች ተፈጥረው፣ ዛሬ ሁሉም ሰው በጣም የተሻሻለና ፈጣን የሆነ ኢንተርኔ ያለው ስልክ በእጁ ይዞ፣ ዛሬ ቴለቭዥን ልክ እንደ ኮምፒተር ብልጥ (SmartTV)ስማርት ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ነው ያለንው።
ታዲያ ከዚህ የበለጠ የተመቻቸ ጊዜ መቼ ይመጣል። ሜዳውም ይኽ ው ፈረሱም ይኽ ው እንዲሉ ቴክኖሎጂና ጊዜ ከምንግዜውም በላይ ተገጣጥመዋል። በዚያው ልክ ድግሞ የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪወች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር አብረው ኢንዲጓዙ ጊዜው በጣም ምቹ ሆኗል። ታዲያ ይህ ጊዜ እኛ ስናልመው እና ስንመኘው የነበረ ጊዜ ስለነበር ያለ የሌለ ኃይላችንን አሰባስበን የኢትዮጵያን ፊልምና ኪነጥበብን ለመጭው ትውልድ ለማስረከብ ቆርጠን ተነስተናል። አላምች ሰፊና እሩቅ ነው ግባችንም ብዙ ስራና መስዋትነትም ይጠይቃል።
ታዲያ ስማችንን ግራር ብለንዋል። ግራር አገር በቀል፣ በጣም መከራ ቻይ፣ ሁሉንም አስተናጋጅ፣ አይበገሬ ዛፍ ነው። የኛ ግራር ዝም ብሎ ግራር አይደለም፣ ያደግንበት፣ የተጫወትንበት፣የተጠለልንበት፣እንደ ምልክት የምንጠቀምበት ታላቅ ግራር ነበር፣ አወ አሁን ግን የለም፣:: አወ ጥቅሙንና ታሪኩን የማያውቅ ሰው/ሰወች ቆረጠው በቦታው መንገድ ሰሩበተ:: ግን ያግራር በዚህ በእኛና በእናንተ ዘላለማዊ ይሆናል።
እኛ ከዚህ ድረ ገፅ የምናቅርባችው መረጃዎች ከዩቱብ እና ከሌሎች የቪዲዮ ማሳያ ድረ ገፆች ላይ ኮዳቸው ብቻ የተቀዳ ነው። ንብረትነታቸው ለእያንዳንዱ ቪዲዮውን ለጫነው ግለስብ ነው። ታዲያ እኛ ቪዲዮውችን ስልጫናቸው አንዳንዴ የጫነው ግለሰብ ከዩቱብም ሆነ ከሌላ ድረ ገፅ ካወጣቸው ቪዲዮወችን ማዬት አትችሉም። ለወደፊቱ ግን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ከዋናው የቪዲዮ ባለቤት ጋር በመተባበር ቪዲዮዎችን ከእኛው ጋ ለማግኝት ትችላላች ሁ። ስራው በቅርብ ይጀምራል። እስከዛው ባለው ተዝናኑ
ስለጎበኛች ሁን ከልብ እናመሰግናለን
ግራር ሚዲያ